المدة الزمنية 6:25

ኤርቱግሩል | Ertugrul | Ertugrul film Amharic | የሞንጎሎች አስገራሚ ታሪክ ክፍል 5

بواسطة ARIF MEDIA
2 876 مشاهدة
0
66
تم نشره في 2021/03/20

#ቲሙር_ኻን ( Tamerlane ) አረመኔው የወረራዎች ሁሉ አባት ወይንስ የኢስላም ሰይፍ ? ---------------------------------------------------------- የሞንጎሎች ታሪክ - ክፍል 5 ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ( Seid Social - ሰኢድ ሶሻል ) እናንተየ እኔንኮ እንደ ሞንጎሎችና ቱርኮች ታሪክ የሚያስደንቀኝ ልቤን ሰቅዞ የሚይዘኝ የለም ። ብቻ አላውቅም በእነርሱ የታሪክ ፍቅር ተማርኪያለሁ ። ስለነርሱ ሳነብ ሳገላብጥ የልብ ትርታየ ይጨምራል በቃ የሆነ ውርር የሚያደርግ ስሜት ይሰማኛል ። እነዚያ የአለምን ታሪክ እስከወዲያኛው የለወጡ ዘላኖችን ባሰብኩ ጊዜ የአላማ ፅናት ያላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ህዝቦች በቢሊዮን የሚቆጠርን የአለም ህዝብ አንበርክከው መግዛት እንደሚችሉ ባወኩ ጊዜ በሀሳብ ወደ ቱርክሜኒስታን ሞንጎሊያ ተራራማ ግዛቶች እነጉዳለሁ ! ዛሬ ደግሞ የምናገራችሁ ስለ ቲሙር ኻን ! ቱርካዊም ሞንጎሊያዊም ስለሆነው ቲሙር ኻን ! ነብያችንንም ጄንጊስ ኻንንም ስለሚወደው አወዛጋቢው የጦር ሊሂቅ ታመርሌን !! ኢስላምንም የሞንጎሎች ስርአትንም ስለሚያፈቅረው ቲሙር ኻን ! የነብያችን ቤተሰብ ( አሊ በይት) ነኝ የጂንጊስ ኻንም ቤተሰብ ነኝ ስለሚለው አሚር ቲሙር !!!! አስፈሪው ቱርኮ-ሞንጎሊያዊ ነጎድጓዳማው አሰገምጋሚ ጦረኛ ቲሙር ታራጋይ ከአባቱ ከአሚር ታራጋይና ከእናቱ ከተኪና ኻቱን እ.ኤ.አ በ 1336 በሰመርቀንድ አካባቢ በአሁኗ ኡዝቤኪስታን ተወለደ ። በርግጥ እርሱ ሲወለድ ሚሊዮኖች ሊያልቁ ተቀድሮላቸው ነበረ። መቼስ ያ የመካከለኛው ኤዥያ ምድር ፤ ያ ከቡኻራ እስከ ሰመርቀንድ ፤ ከሬይ እሰከ ኢስፋሃን ፤ ከ ተብሪዝ እስከ ኢስፋሃን ፣ ከነይሳቡር እስከ ኡርጌንች ፣ ከባግዳድ እስከ ሞሱል ኧረ ስንቱ ያላበቀለው አሊም ፣ ወራሪ ፣ የአላህ ባሪያ ፣ የአላህ ባሮች ጨፍጫፊ ፣ ሳይንቲስት ፣ የደም ጠጭ የለም!! ያ ምድርኮ ግርርም ይላል ! የአሚሩ ልጅ ቲሙር አስተዳደጉ አስገራሚ ነው ። እርሱ ከልጅነቱ ጀምሮ የጦር መሪ ነበር ። ግና በልጅነቱ የሚመራው ሀገርን የሚያስተዳደር ጦር ሳይሆን በሌብነት በጣም የተካኑ የዘራፊዎችን ቡድን ነው ። ይህ በቲሙር የሚመራው ቡድን እጅግ አደገኛ እጅግ ስልታዊ እጅግም የተራቀቀ የሌባ ቡድን ነው ። አንድ ጊዜ እንደለመደው ይህን ቡድን ይዞ ከበግ አርቢዎች በጎችን ሊዘርፍ ይመሽጋል ። ግና ያኔ በለስ አለቀናውምና በበግ ጠባቂዎቹ ጦረኞች የቀስት ሲሳይ ሆነ ። እናም እግሩ በሁለት ቀስት ተመታ ሁለት የእጆቹ ጣቶችም ተቆረጡ ። ያ የደረሰበት ጉዳት በህይወቱ ሙሉ የሚለቀው አልሆነም እናም የእግሩን ሺባነት ለመግለፅ በፐርሺያ ታመር ሌንግ አሉት ። ፈረንጆቹ ደግሞ Tamer lane አሉት ።Tamer The lame ከሚለው የተወሰደ ነው ። Lame ማለት ሺባ አንካሳ እንደማለት ነው ። Timr ( ቲሙር ) ማለት በቱርክኛ ብረት ማለት ነው ። የቲሙር አፍ መፍቻ ቋንቋ ቱርክኛ ነው ። ራሱንም ቱርካዊ መሪ እንደሆነ ነው የሚያየው ። ለነገሩ ቁረይሻዊ ነኝ ማለቱንስ ማን ይዞበት ! ቲሙር ከወንበዴዎች መሪነት ቀስ በቀስ ወደ ቱርኮ-ሞንጎሎቹ የኢልኻኔት ጦር አመራር ውስጥ እየሰረገ እየሰረገ መግባት ያዘ ። በዚያም በራሱ የሚመራውን የቱርኮች ጦር ማደራጀት ቻለ ። በሞንጎሎች የስልጣን ሽሚያና መራኮት ውስጥ የራሱን ተፅእኖ እያገዘፈ ሀይለኛው መሪ ለመሆን ቻለ ። ግና ቲሙር ኻን መሆን አይችልም ምክንያቱም የጂንጊስ ኻን ተወላጅ አይደለም ። በሞንጎሎች ባህል ኻን የሚሰጠው ለጂንጊስ ተወላጅ ነው ። ቲሚር የጂንጊስ ጎሳ አባል ቢሆንም እንደነ በርኬ ኻን ከጂንጊስ አይወለድም ። ስለዚህ ከጂንጊስ ተወላጅ የሆነን ሰው የይስሙላ ኻን አድርጎ የቻጋታይ ኻኔትን ተቆጣጠረ ። ቲሙር ኸሊፋም ሊባል አልተቻለም ። ምክንያቱም የነብያችን ሶ.ዐ.ወ ቤተሰብ አልነበረም ። እናም ሌላ አፈታሪክ ማስነገር ጀመረ ። እርሱ አላህ የፈጠረው ልዩ ሰው መሆኑን ! ይህ አልበቃውም " እኔ የታላቁ ሶሃባ የአሊ ቢን አቢጧሊብ የመንፈስ ተወላጅ ነኝ "አለ - አህለል በይት ! እንደማንም ቲሙር የቻጋታይን ኢምፓየር አተቆጣጠረ በሗላ ወረራውን አጠናክሮ በመቀጠል አብዛኛው ኤዥያን መካከለኛው ምስራቅን እስከ ምስራቅ አውሮፓ ብሎም እሰከ ሩሲያ ተቆጣጠረ ። ዘመቻውን #ጂሃድ በማለት አወጀ ። እራሱንም " የጋዚዎች መሪ " አሚረል ሙእሚኒን አለ ። ቲሙር ለራሱ የኢስላም ሰይፍ ( ሰይፉል ኢስላም ) የሚልን ማእረግ ሰጠ ። Sword of Islam , Conquer of the World ! አሚር ቲሙር የተቆጣጠራቸውን ሙስሊም ያልሆኑ የግዛት መሪዎች ሁሉ እንዲሰልሙ አዘዘ ። አሚር ቲሙር የአሁኖቹን ኢራቅ ፣ ኢራን ፣ አፍጋኒስታን ፣ ፓኪስታን ፣ ህንድ ፣ አዘርባጃን ፣ ጆርጅያ ፣ አርሜኒያ ፣ ኡዝቤኪስታን ፣ ታጂኪስታን ፣ ኪርጊስታን ፣ ቱርክሜኒስታን ፣ የቱርክን ብዙ ክፍሎች ፣ ሶሪያን ጠቅልሎ የያዘ እጅግ ሰፊ መንግስት ነበር የመሰረተው ። እርሱ የአሚር ልጅ አሚር ነበረ ። ለጅሃድ ክተት ጠርቶ ያላሸነፈው ዘመቻ የለም ። የህንድ ሱልጧኔትን አፈራረሰው ። በህንድ ዘመቻ ሂንዱዎች ላይ በከፈተ ጊዜ ሂንዱዎችን መጨፍጨፍ ጅሃድ ነው ንበረቶቻቸውን አማልክቶቻቸውን አውድሙ ኢስላም ብቻ ሂንድን እንዲገዛ አድርጉ በኢስላም ጠላቶች ላይ የሰላ ሰይፎቻችሁን ምዘዙ አለ ። አዎ እርሱ ከህንድ እስከ ሩሲያ አንበርክኮ አንቀጥቅጦ የገዛ ምትሃታዊ ሰው ነበር። እርሱ ሩሲያን ለመውረር በተዘጋጀ ጊዜ ኦርቶዶክሷ ሩሲያ ብርክ ያዛት ። የሩሲያው የጊዜው መሪ "ታላቁ " ቫሲሊ ቀዳማዊ በጦርነት አሚር ቲሙርን ሊገጥመው እንደማይችል በመረዳት በሩሲያ የሚገኙ ጳጳሳትንና ህዝበ ኦርቶዶክስን ለፀሎት ክተት ጠራ ! ምእመናኑም ተሰልፈው " ኦ ወላዲተ አምላክ ! እባክሽን የሩሲያን ምድር ጠብቂያት " እያለ ፀለዩ ! አሚር ቲሙር እንደዚህ አይነት አስፈሪ መሪ ነበር ። አሚር ቲሙር በአጠቃላይ በፈፀማቸው ወረራዎች 17 ሚሊዮን ሰዎች ተገድለዋል ። ያ ማለት በጋዜው ከነበረው የአለም ህዝብ 5 % የሚሆነው በታመርሌን ተገድሏል ማለት ነው ። ሞንጎሎች በሺዎች የሚቆጠር ህዝብ መግደል አይመቻቸውም በሚሊዮን እንጅ! ክብሯን አንባቢዎቼ ለዛሬ በዚህ ይብቃን ! በቀጣዩ የአሚር ቲሙር ( ታመርሌን ታሪክ ) 👉 ከኦቶማኑ ሱልጧን ከቤይዜድ ቢን ሙራድ ቢን ኦርሃን ቢን ኡስማን ቢን አርቱግሩል ጋር ያደረገውን የአንካራ ጦርነትና በኦቶማን ኢምፓየር ላይ ያደረሰውን ውድመት 👉 አሚር ቲሙር ለኢስላም ያደረገውን አስተዋጽኦ ፤ በሙስሊሞች ላይም ያደረገውን ጭፍጨፋ 👉 የአሚር ቲሙርን ፍፃሜና የተተኪዎቹን ሁኔታ እንቃኛለን! ወቢላሂ አትተውፊቅ ! #Seid_Mohammed_Alhabeshiy Ertugrul | ኤርቱግሩል | በአማረኛ ትርጉም | የሞንጎሎች ታሪክ ክፍል 5 | ታመርሌን

الفئة

عرض المزيد

تعليقات - 10