المدة الزمنية 19:55

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ የመሬት ችግር አለ ብዬ አላምንም›› ኢ/ር ፀደቀ ይሁኔ

74 مشاهدة
0
2
تم نشره في 2023/07/29

ፕሬሱን መደገፍ ሀገርን መደገፍ ነው!!! መጽሔት እና ጋዜጣችን ከገበያ ውጪ ከመኾኑ በፊት ድጋፍዎን ያድርጉልን በከፈትነው የጎፈንድሚ አካውንት (https://www.gofundme.com/f/Support-fekadu-the-ethiopian-freepress-champ) በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ታሪክ ላለፉት ከ25 ለላቁ ዓመታት ሀገራችንን እና ሕዝባችንን ስናገለግል ቆይተናል፡፡ በእነዚህ ዘለግ ያሉ ዓመታት ባጋጠሙን ውጣ ውረዶችም ለንባብ ካዋልናቸው የሕትመት ውጤቶች መሃል ሁለት ጋዜጦች እና ሦስት መጽሔቶች ከየትኛውም ተቋማት ማስታወቂያ እንዳናገኝ ክልከላን ከማስተናገድ ጀምሮ እስከ መዘጋት የደረሰ ዕጣን ተቀብለናል፡፡ ይኽ ያለማቋረጥ ይከተለን የነበረውን ተደጋጋሚ እሥርና ድብደባንም ይጨምራል፡፡ በዚህ ሁሉ መራር መሥዋዕትነት ውስጥ አልፈን ዛሬ ብንደርስም አሁንም በበርካታ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት መጽሔታችን “ግዮን” እና ጋዜጣችን “ኢትዮ ሐበሻ” ከሕትመቱ ሚዲያ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የመውጣት ዕጣ ተጋርጦባቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ባለችበት አሁናዊም ኾነ ዘላቂ እውነታ፣ ትክክለኛውን የአራተኛ መንግሥት አካልነት ሚናውን የሚወጣ ሀቀኛ እና ሚዛናዊ መረጃን ለአንባቢ የሚያደርስ የፕሬስ ውጤት ያስፈልጋል፡፡ ስለኾነም በመላው ዓለምና በሀገራችን የምትገኙ የነጻ ፕሬስ ወዳጆች በጎፈንድሚ እና በዐይነት የቀረበላችሁን የድጋፍ ጥሪ በመቀላቀል አጋርነታችሁን እንድታሳዩን እንጠይቃለን፡፡ በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ታሪክ ግዴታቸውን የተወጡና እየተወጡ በሚገኙ ጋዜጠኞች የሚዘጋጁ የሕትመት ውጤቶች!

الفئة

عرض المزيد

تعليقات - 0